=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ጥራዝ 1, መጽሐፍ 1 የሐዲስ ቁጥር 1 እና መጽሐፍ 2,ቀጥር 51
ኡመር ኢብኑ አል-ኸጧብ እንደተረከው
የአሏህ መልእክተኛ: የስራዎች ምንዳ በኒያ ይወሰናል። እያንዳንዱም ሰው ባሰበው ነገር ይመነዳል። እናም ለዓለማዊ ጥቅም ወይም ሴት ለማግባት ብሎ የተሰደደ ስደቱ ለተሰደደበት ነገር ነው» ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ።
ጥራዝ 1,መጽሐፍ 2,ቁጥር 7
ኢብኑ ኡመር እንደተረከው
የአሏህ መልእክተኛ: ኢስላም በሚከተሉት አምስት መርሆዎች መሠረት ነው ብለዋል:-
1) ከአሏህ ውጭ ሊመለክ የሚገባው ነገር አለመኖሩንና ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ መልእክተኛ መሆናቸውን መመስከር
2) ሶላት መስገድ
3) ዘካ መስጠት
4) ሐጅ ማድረግ
5) የረመዷንን ወር መፆም
ጥራዝ 1, መፅሐፍ 2, የሐዲስ ቁጥር 8
አቡሑረይራ እንደተረከው
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ): «ኢማን ከ60 ቅርንጫፎች በላይ አሉት። ይሉኝታም አንዱ የኢማን ክፍል ነው» ብለዋል።
ጥራዝ 1, መጽሐፍ 2, የሐ.ቁጥር 9
አብዱሏህ ቢንአምር እንደተረከው
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል: «ሙስሊም ማለት ሙስሊሞችን በምላሱና በእጁ የማይጎዳ የሆነ ነው። ስደተኛ ማለት ደግሞ አሏህ ከከለከለው ነገር የተከለከለ ነው» ብለዋል።
ጥራዝ 1, መጽሐፍ 2, የሐ.ቁጥር
አቡ ሙሳ እንደተረከው
የተወሰኑ ሰዎች የአሏህ መልእክተኛን እንዲህ ሲሉ ጠየቇቸው:- የማን ኢስላም ነው ከሁሉም በላጩ? (i.e ያም ማለት በጣም ጥሩ የሆነው ሙስሊም ማነው?) እሳቸውም ሙስሊሞችን በምላሱና በእጁ ከመጉዳት የራቀ (ያስወገደ) ነው ሲሉ መለሱ።
ጥራዝ 1, መጽሐፍ 2, የሐ.ቁጥር 12
አነስ እንደተረከው ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ:-
አንዳችሁም አላመናችሁም ከናንተ መካከል ለራሱ የወደደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ።
ጥራዝ 1, መጽሐፍ 2, የሐ.ቁጥር 13
አቡሑረይራ እንደተረከው የአሏህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል:-
ሂወቴ በእጁ በሆነችው አንዳችሁም እምነት የላችሁም (አላመናችሁም) ከናንተ መካከል ከአባቱና ከልጁ አብልጦ እስካል ወደደኝ ድረስ።
ጥራዝ 1, መጽሐፍ 2, የሐ.ቀጥር 15
አነስ እንደተረከው
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል:-
የሚከተሉት ባህሪያት ያሉት የእምነት ጥፍጥና ይኖረዋል ብለዋል
1) አሏህና መልእክተኛው ከማነኛውም ነገር በላይ ውድ የሆኑለት
2) ሰውን የሚወድና ውዴታውም ለአሏህ ብሎ የሆነ
3) ወደ ጀሃነም እሳት መወርወርን እንደሚጠላ ሁሉ መጥመምን(መክፈርን) የሚጠላ የሆነ
ጥራዝ 1 መጽሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 169
አኢሻ(ረ.ዐ) እንደተረከችው ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ጫማ ሲለብሱ ፣ ፀጉራቸውን ሲያበጥሩ ፣ ሲያፀዱ ወይም ሲታጠብና ማንኛውንም ነገር ሲያደርጉ በቀኝ ጐናቸው መጀመር ይወዱ ነበር።
ሰሒህ አል-ቡሐሪ የሐ.ቁጥር 527
ኢብን ኡመር(ረ.ዐ) እንደተረከው የአሏህ መልእክተኛ(ሰ.ዐ.ወ): "የአስር ሶላትን ሆንብሎ(አውቆ) ያመለጠው ሰው ቤተሰቡንና ንብረቱን እንዳጣ ሰው ነው።" ብለዋል።
ኢማሙ አህመድ ኢብን ሐምበል ጥራዝ የሐ.ቁጥር
አቡቀትዳህ(ረ.ዐ) እንደተረከው ነብዩ እንድህ ብለዋል
"ክፉ ሌባ ከሶላቱ የሚሰርቅ ነው። ያረሱ ሉሏህ! የሶላት ሌባ ማነው? ሲሉ በትህትና ጠየቇቸው። ሩኩኡን ወይም ሱጁዱን በትክክል የማያከናውን ነው።" ሲሉ መለሱ።
ሰኺህ አል-ቡኻሪ የሐ.ቁጥር 527
ኢብን ኡመር(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው
የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ): የአስር ሶላት ሆንብሎ(አውቆ) ያመለጠው ሰው ልክ ቤተሰቡንና ሃብት ንብረቱን እንዳጣ ሰው ነው ብለዋል።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 169
አኢሻ(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ): ጫማ ሲለብሱ ፀጉራቸውን ሲያበጥ__ ሲያፅዳዱ ወይም ሲታጠቡና ማንኛውንም ነገር ሲያደርጉ በቀኝ ጎናቸው መጀመር ይወዱ ነበር።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 170
አነስ ቢን ማሊክ እንዳስተላለፈው
የአሏህ መልዕክተኛን(ሰ.ዐ.ወ) አይቻቸዋለሁ የአሰስር ሶላት በደረሰ ጊዜ ሰዎች ውዱዕ ለማድረግ ውሃ ፈለጉ ነገርግን ማግኘት አልቻሉም። ብላ ላይ የውዱዕ ውሃ ለአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) መጣላቸው፤ እጃቸውንም ማሰሮው ውስጥ አስገቡትና ሰዎች ከርሷም ውዱዕ እንዲያደርጉ አዘዙ። ሁሉም ውዱዕ እስኪያከናውኑ ድረስ ከጣታቸው ስር ውሃ ሲፈልቅ አይቻለሁ።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 172
አነስ(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው
የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) እራሳቸውን በተላጩ ጊዜ የተወሰነ ፀጉራቸውን ቀድሞ በመጀመሪያ የወሰደው አቡ ጦልሃ ነበር።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 177
አባስ ቢን ተሚም እንዳስተላለፈው
አጎቴ የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) አንድ ሰው ሶላቱን ትቶ መሄድ የለበትም ድምፅ እስካልሰማ ወይም የሆነ ነገር እስካልሸተተው ድረስ ብለዋል ብሏል።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 207
ጃዕፈር ቢን ኡመያ እንዳስተላለፈው
አባቴ እንዲህ ብሏል የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ከትከሻው አካባቢ የሆነ የበሰለ የበግ ስጋ ሲበሉና ለሶላት ሲጠሩ ቢለዋቸውንም አስቀምጠውና ውዱዕ ደግመው ሳያደርጉ ሲሰግዱ አይቻቸዋለሁ ብሏል።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 209
መይሙና(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ከትከሻው አካባቢ የሆነ የበግ ስጋ በሉና ውዱ ደግመው ሳደርጉ ሰገዱ።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 211
አኢሻ(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው
የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ከእናነተ መካከል አንዳችሁ እየሰገደ የመጫጫን ስሜት ከተሰማው የመጫጫኑ ስሜት እስኪያበቃለት ወደ አልጋው ይሂድ(ይተኛ)። ምክኒያቱም እንቅልፍ ተጫጭኖት እያለ የሚሰግድ ሰው ለራሱ ምህረትን ወይም መጥፎ ነገር እየለመነ እንደሆነ አያውቅምና ብለዋል።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 212
አነስ እንዳስተላለፈው
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ከናንተ መካከል አንዳችሁ እየሰገደ የመጫጫን ስሜት ከተሰማው የሚናገረውን(የሚቀራውን) ነገር እስኪረዳ ድረስ ይተኛ ብለዋል።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 216
አነስ ቢን ማሊክ እንዳስተላለፈው
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ለተፈጥሮ ጥሪ መልስ ሊሰጡ(ሊፅዳዱ) በሄዱ ጊዜ ብልታቸውን የሚያፀዱበት ውሃ አመጣላቸው ነበር።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 218-219
አነስ ቢን ማሊክ እንዳስተላለፈው
አንድ የአረብ ዘላን መስጅድ ውስጥ ሲሸና ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) አዩትና ሰዎች እንዳይረብሹት (እንዳያቇርጡት) ነገሯቸው። በጨረሰ ጊዜ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ውሃ እንዲያመጡላቸው ጠየቁና ከሽንቱ ላይ አፈሰሱበት።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 228
አኢሻ(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው
ፋጢማ ቢንት አቢ ኹበይሽ ወደ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) መጣችና እንዲህ አለች የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! ቀጣይነት ያለው(ያልተቇረጠ) ደም ከማህፀኔ ይፈሰኛልና አልነፃ አልኩ ሶላቶቼን መተው አለብኝን? አለቻቸው። የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) አይሆንም(ልትተይ) አይገባም። ምክኒያቱም ከደም ቧንቧሽ እንጅ ሃይድ አይደለም። የወር አበባሽ ሲመጣብሽ ሶላትሽን ተይ እናም ሲጨርስ ደሙን ታጥበሽ ሶላትሽን ስገጅ አሏት።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 237
መይሙና እንዳስተላለፈችው
አይጥ ያረፈችበትን(የወደቀችበትን) ቅቤ በተመለከተ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ተጠይቀው አይጧንና በዙርያዋ ያለውን ቅቤ ጥላችሁ የቀረውን ተጠቀሙ ብለዋል።
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ማንኛውም ልጅ የሚወለደው ንፁህ ከሆነ የተፈጥሮ ባህሪ ጋር ነው። ወላጆቹ አይሁዳ ፣ ክርስቲያን ፣ ማዝዲስት እንዲሆን ሊቀይርት ይችላሉ ብለዋል።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 238
አቡ ኹረይራ እንዳስተላለፈው
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) በአሏህ መንገድ የቆሰለ ሙስሊም በግጭት ጊዜ ጉዳት እንደደረሰበት ሆኖ በዕለተ ትንሳኤ ይቀሰቀሳል፤ ደሙም ከቁስሉ ይፈሳል፤ ቀለሙም የደም ቀለም ይሆናል። ነገርግን ልክ እንደ ሚስክ ይሸታል ብለዋል።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 241
አብዱሏህ ቢን መስዑድ እንዳስተላለፈው
አንዴ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ካዕባ ውስጥ ሶላት እየሰገዱ እያለ አቡ-ጀህል ከባልደረባዎቹ ጋር ተቀምጦ ነበር። ከመካከላቸው አንደኛው ለሌሎቹ ከናንተ መካከል ማነው የግመል ፈርስ የሚያመጣና ሙሐመድ ሱጁድ ባደረገ ጊዜ ከጀርባው ላይ የሚደፋበት አለ። ከእነሱም መካከል እድለቢስ የሆነው ተነሳና ይዞ መጣ። ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ሱጁድ እስኪያደርጉ ድረስ ጠበቀና በትከሻዎቻቸው መካከል ደፋባቸው። እየተመለከትኩ ነበር ሆኖም ግን ምንም ነገር ማድረግ አልቻልኩም። ከኔጋ ሰዎች ቢኖሩና ብቇቇማቸው ተመኘሁ። እርስ በእርሳቸውም ላይ እየወደቁ መሳለቅ ጀመሩ። የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ሱጁድ እያደረጉ ነበርና ፋጢማ(ረ.ዐ) መጥታ ፈርሱን ከጀርባቸው አንስታ እስክትጥለው ድረስ እራሳቸውን አላነሱም ነበር። እራሳቸውን ቀና አደረጉና ሶስቴ አሏህ ሆይ! ቁረይሽን ቅጣ አሉ። እናም ለአቡ-ጀህል እና ለአጋሮቹ ፈታኝ ነበር። ነቡዩ(ሰ.ዐ.ወ) አሏህን በነሱ ላይ በለመኑ ጊዜ በዚህ ከተማ መካ ውስጥ የሚሰገድ ሶላት እና ዱአ ተቀባይነት እንደሚያገኝ የፀና እምነት ስለነበራቸው ፈሩ።
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) አሏህ ሆይ! አቡጀህልን ፣ ኡትባ ቢን ራቢያ ፣ ሸይባ ቢን ራቢያ ፣ አልወሊድ ቢን ኡትባ ፣ ኡመያ ቢን ኸለፍ እና ኡቅባ አል-ሙይጥ እና ሌሎች ስማቸውን የማላስታውሳቸው ጨምሮ ነፍሴ በእጁ በሆነችው በአሏህ ይሁንብኝ! በአሏህ መልዕክተኛ ሲቆጠሩ የነበሩ ሰዎችን አስክሬን በቀሊብ አይቻለሁ(i.e ቃሊብ ከበድር ግድግዳዎች አንዱ ነው።)
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 243
አኢሻ(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ስካር የሚፈጥሩ መጠጦች ሁሉ ሐራም ናቸው ብለዋል።
ጥራዝ 1 መጽሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 246
ኹዘይፋ(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ሌሊት በተነሱ ጊዜ አፋቸውን በሲዋክ ያፀዱ ነበር።
ጥራዝ 1 መጽሐፍ 5 የሐ.ቁጥር 255
ኢብን አብዱሏህ እንዳስተላለፈው
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እራሳቸው ላይ ሶስት ጊዜ ውሃ ያፈረሱ ነበር።
ጥራዝ 1 መጽሐፍ 5 የሐ.ቁጥር 262
አኢሻ(ረ.ዐ) እናዳስተላለፈችው
የአሏህ መልዕክተኛ የጀናባ ትጥበት ባደረጉ ጊዜ እጃቸውን መጀመሪያ ይታጠቡ ነበር።
ጥራዝ 1 መጽሐፍ 5 የሐ.ቁጥር 284
አቡ ሰላማ(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ጁኑብ ሆነው እያለ ይተኛሉ? ስል አኢሻን ጠየኴት። አዎ! ነገርግን ወደ አልጋ ከመሄዳቸው በፊት ውዱዕ ያደርጋሉ ስትል መለሰችልኝ።
ጥራዝ 1 መጽሐፍ 5 የሐ.ቁጥር 285
ኡመር ቢን አል-ኸጧብ እንዳስተላለፈው
የአሏህ መልዕክተኛ ከኛ መካከል አንዱ ጁኑብ ሆኖ ያለ መተኛት ይችላን? ስል ጠየኴቸው። ውዱእ ካደረገ አዎ! ጁኑብ እንኴ ቢሆን መተኛት ይችላል ሲሉ መለሱልኝ።
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል አንድን ሰው መልካም እንዲሰራ ያመላከተ ሰው መልካም እንደሰራው ሰው ተመሳሳይ ምንዳ ያገኛል ብለዋል።
በቡኻሪ እንደተዘገበው
የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ከናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ነው ብለዋል።
ሰሂህ አል-ቡኻሪ የሐ.ቁጥር 667
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) አሏህ ሰዎችን በሃይማኖታቸው ጉዳይ የሚጠቅምበት የሆነን እውቀት የሸሸገ(የደበቀ) ሰው በዕለተ ትንሳኤ አሏህ ከጀሃነም እሳት በሆነ ልጏም ይለጉመዋል ብለዋል።
ኢብን መስኡድ እንዳስተላለፉት
የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) አንድ መስመር አሰመሩና ይህ የአሏህ መንገድ ነው አሉ። እናም በግራና በቀኝ ሌሎች መስመሮችን ቅርንጫፍ አውጥተው አሰመሩና እነዚህ በመጨረሻው ሸይጧን ህዝቦችን የሚጣራባቸው መንገዶች ናቸው አሉ።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|